ኣማርኛ / Amharisch

ከቀኝ ዘመም፣ የዘረኞች ወይም ፀረ-ሴማውያን ጥቃት በኋላ ምን ማድረግ አለብዎት?

response በመላው የሄሴ ፕሮቪንስ ውስጥ የሚሰራ ለእነዚህ የጥቃት ሰለባዎች የድጋፍ፣ የማጀብና የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ነው

  • ከቀኝ ዘመም፣ የዘረኞች ወይም ፀረ-ሴማውያን ጥቃት ሰለባዎች

  • ዘመዶች

  • ጓደኞች

  • ደጋፊዎች

  • ምስክሮች

response እንዴት ሊረዳዎ ይችላል?

response አስፈላጊ ከሆነ በግል፣ በሚስጥርና ማንነት ሳይገለጽ እና በመላው የሄሴ ፕሮቪንስ ውስጥ የሳይት/ቦታ ላይ የምክር አገልግሎት ያቀርባል።

የምክር አገልግሎቱ በነጻ ይሰጣል። አስፈላጊ ከሆነ አስተርጓሚርጓሚዎች እንመድባለን

ከምናቀርባቸው አገልግሎቶችም መካከል የሚከተሉትን ይገኙበታል

  • የኦንላይን እና/ወይም የገጽ ለገጽ ውይይቶች

  • በካሳ ክፍያዎች ላይ ማገዝ

  • ጥያቄ ሲያቀርቡ በቀጠሮዎችዎ ላይ ከእርስዎ ጋር አብሮ መገኘት

  • ጥያቄ ሲቀርብለት የህዝብ ግንኙነት ስራዎች መስራት

responseን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

የግንኙነት መረጃችን

የFrankfurt am Main ጽ/ቤት

kontakt@response-hessen.de

069 - 348 770 530

የKassel ጽ/ቤት

kassel@response-hessen.de

0561 - 729 897 00